የወረዳዉ ማህበረሰብ ባህላዊ እሴቶችና የመስህብ ሀብቶች ባህል የአንድን ማህበረሰብ የአኗኗር ዘይቤ ፣አስተሳሰብና በአንድ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ አዉድ ዉስጥ ያለዉን ልምድና ባህሪ የሚገልጽ በአጠቃላይ ቁሳዊና ህሊናዊ ሀብቶቹን የሚያካትት ሰፊ ጽንሰ ሀሳብ እንደሆነ በርካታ የዘርፉ ምሁራን ይስማሙበታል፡፡ የኢፌዲሪ መንግስት ጥቅምት 1990 ዓ.ም ባወጣዉ የባህል ፖሊሲ በገጽ 5 ላይ ስለ ባህል የሚከተላዉን ያስቀምጣል ፡፡ «..ባህል የሰዉ ልጅ ሰብዓዊና ምክንያታዊ ፍጡር እንዲሆን ያስቻሉት ወይም ከሌሎች ፍጡራን ለመለየት ያበቁት ማንኛዎቹም ምሁራዊ ስነ ምግባራዊ ፣አካላዊ ፣ቴክኒካዊና በአዕምሮ እዉቀት ራሱን የማሰልጠን ሁኔታዎች የሚያጠቃልል ጽንስ ሀሳብ ነዉ፡፡ እንዲሁም አንድ ህዝብ ከሌላዉ ተለይቶ የሚታወቅባቸዉን ሁኔታዎች ማለትም የአኗኗር ዘይቤዎቹን ፣እምነቶቹን ትዉፊቶቹን ፣በአጠቃላይ ቁሳዊና ህሊናዊ ሀብቶቹን የሚያካትት ሰፊ ጽንስ ሀሳብ ነዉ፡፡» የሚል ነዉ፡፡ ይሄ ትርጓሜ ከወረዳዉ ብሔረሰቦችና ህዝቦች አንጻር ሲታይ የእነዚህ የባህል ሀብቶች ባለቤት ሲሆን አንዳቸዉ ከአንዳቸዉ የሚለዩበትን ማህበራዊና፣ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊ ፣አስተዳደራዊ /ህጋዊ/ ስነ ምግባራዊ ሀይማኖታዊና ስነ ልቦናዊ ሁኔታዎችን ወይም ቋንቋዎቻቸዉን፣ታሪክና ስነ ቃሎቻቸዉን ፣ቤት አሰራራቸዉን ፣የማምረቻ መሳሪያዎቻቸዉንና አመጋገባቸዉን ፣ልብስና አለባበሳቸውን፣አጋጊያጣቸውንና የስነ ውበት ግንዛቤያቸውን ፣ሀይማኖታዊና የእምነት ክንዋኔዎቻቸዉን፣ ከወሊድ ከሠርግና ከሞት ጋር የተያያዙ ስርዓቶቻቸዉን ፣በዝምድና በጉርብትናና በሌሎች ግንኙነታቸዉ ላይ የተመሰረተ መተጋገዝና መተሳሰባቸዉን፣ባህላዊ የአስተዳደር ዘይቤያቸዉን ፣ባህላዊ የጤና እንክብካቤ ዘዴዎቻቸዉና ሌሎችንም ሁሉ የሚያጠቃልል ነዉ፡፡ እንዲሁም የወረዳዉን ህዝቦች ቅርሶች ፣ስነ ጥበባትና ዕደ ጥበባት ፣ልዩ ልዩ ትዉፊቶች ፣ጭፈራ ፣ዉዝዋዜና ዘፈኖቻቸዉ ፣ንግድ ትምህርት በብሔረሰቦቹ የሚከበሩ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ክብረ በዓላትና ባህላዊ ትዕይንቶች ይካተታሉ፡፡ እነዚህን የወረዳዉን ህዝቦች የተለያዩ የባህል እሴቶች ቁሳዊና መንፈሳዊ የባህል ዕሴቶች በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ከፍለን ማየት ይቻላል፡፡ የወረዳዉን ህዝብ ቁሳዊ ባህል ሲባል የሚታዩ ነገሮች ፣መገልገያ መሳሪያዎችን ፣ግንቦችን/ልዩ ልዩ የቤት አሠራሮችን/፣ታሪካዊ እቃዎችን እና ቦታዎችን ወዘተ.. የሚያካትት ሲሆን መንፈሳዊ ባህል ሲባል ደግሞ ፖለቲካዉን ፣ሙዚቃቸዉን፣ግጥሙን ፣ትምህርቱን ፣ሃይማኖቱን ፣ወጎቹንና ልማዶቹን ወዘተ… የሚያካትት ነዉ፡፡ እነዚህ የወረዳ ህዝብ ሀብቶች ከትዉልድ ትዉልድ ሲተላለፉ የኖሩ አሁንም፣ በመተላለፍ ላይ ያሉ ህዝቡ በተለያየ ጉዳዮችና ነገሮች የተለየ ስያሜ በመመስረት በስምምነት የሚግባባቸዉና የሚጠቀምባዉ ሀብቶች ናቸዉ፡፡ ከዚህ በመነሳትም የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከሌላዉ የሚለዩበት ፣ዝንባሌያቸዉን ፣ባህሪያቸዉን እና የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያስተካክሉበት እና ተፅዕኖ የሚያሳርፉበት የራሳቸዉ የሆነ የተለየ ባህል አላቸዉ፡፡ የወረዳዉ ህዝብ የእነዚህ ከላይ ቁሳዊና መንፈሳዊ ባህሎች በማለት የተገለፁት የባህል ዕሴቶች ባለቤት ሲሆን ህዝቡ እነዚህን ባህሎች የሚያከናዉንበት የራሱ ታሪካዊና ባላዊ የአከዋወን ስርዓት አለዉ፡፡ እነዚህን የተለያዩ ባህላዊ እሴቶች ስናይ ከቀበሌ ቀበሌ የሚለያዩና ሁሉም ባህላዊ እሴቶችና መስህቦች የወረዳዉን ህ/ሰብ አኗኗር ስርዓቱን ፣ማንነት ፣የህዝቡን ጥበብ ፣የሰዉ ልጅ ላይ መልሶ እንዲያንፀባርቅ የማድረግ ችሎታቸዉን የሚያሳዉቁበትና ሰዉ በስብዕናዉ የተሟላ መሆኑን የሚያዉቁበትን ፣ህዝቡ በማህበራዊ ህይወቱ አግባብ ባለዉ አስተያየት ፍርድ የሚሰጥበትን /የአበጋር የባህላችን ዳኝነት ስርዓት/ አግባብ፣ ከሌሎች ህዝቦችና የጎረቤት አከባቢያቸዉ ጋር ያለዉን ባህላዊ ትስስርና ማህበራዊ ግንኙነት ምን እንደሚመስል በትክክል የሚገልጹ ናቸዉ፡፡ እነዚህ የወረዳዉ ህዝብ የባህል እሴቶችና ሀብቶች ለልማት ካላቸዉ አጋዥነት አንዱ የቱሪዝምን እድገት እንቅስቃሴና በርካታ የቱሪዝም ሀብቶችን በማሰስ ፣በማጥናትና በማስተዋወቅ የቱሪስት ፍሰትን ቁጥር በመጨመር ወረዳዉ ከቱሪዝም እንዱስትሪ ተጠቃሚ እነዲሆን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም እነዚህ የወረዳዉ ባህላዊ ሀብቶች /ባህላዊ አለባበስና አጋጊያጥ ፣ባህላዊና ሀይማኖታዊ ክብረ በዓላት ፣ባህላዊ ክንዋኔዎች ማለትም የአበጋር የዳኝነት ስርዓት ፣ቦለቀያ የሴቶች የዉበት ሳሎን ፣የባህላዊ ምግቦች አመጋገብ ፣ባህላዊ የቤት አሰራር ፣ባህላዊ የመገልገያ ቁሳቁሶች ወይም የዕደ ጥበብ ዉጤቶች ፣ባህላዊ ዘፈኖች፣ጭፈራዎችና ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች /ማህበራዊ ግንኙነትና ትስስር መግለጫ አዉዶች /ሠርግ ለቅሶ /፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረዳጃ ተቋማት ኪነ ጥበብ ለወረዳዉ የገጽታ ግንባታ አንዱና ዋነኛ ታሪካዊ የባህል መግለጫዎች ናቸዉ፡፡ ከነዚህ ሀብቶች ወረዳዉ ጭስ አልባ እንዱስትሪ በመባል ከሚጠራዉ የዘመናችን የቱሪዝም እንዱስትሪ ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ሲችል አሁን ካለዉ ነባራዊ ሁኔታ ግን ከዘርፉ የሚገኘዉ ገቢ ዝቅተኛ ነዉ፡፡ ስለሆነም እነዚህን የወረዳዉን ታሪካዊና ባህላዊ የመስህብ ሀብቶችን ትኩረት ሰጥቶ በማልማት ረገድ ገና ሰፊና ትልቅ ጥረትን የሚጠይቅ የወረዳዉ ህዝብና የመንግስት አካላት የወደፊት የቤት ስራ ናቸው ፡፡ እነዚህን ከላይ ያየናቸውን የወረዳዉ ባህላዊ እሴቶችና የመስህብ ሀብቶች የሚከወኑበትንና ባህላዊ የአከዋወን ስርዓት ከዚህ በታች እንደሚከተለው ዘርዘር በማድረግ ለማቅረብ ተሞክሯል ፡፡
1. የዕደጥበብ ውጤቶችና ባህላዊ መገልገያ ዕቃዎች የወረዳዉ ብሄረሰቦች የራሳቸውን የፈጠራ ችሎታ የሚለኩና ልዩ የሚያደርጓቸውን በርካታ ቁሶችን አምርተው የመጠቀም ልምድ አላቸው ፡፡ በዚህም የተነሳ ወረዳዉ በርካታ የእደጥበብ ሀብቶች ባለቤት ነው፡፡ ከነዚህም መካከል የሽመና እና የዕደ ጥበብ ስራ ዉጠቶች ይጠቀሳሉ፡፡ የረጅም ጊዜ ዕድሜ ያላቸዉ የጥበብ ስራዎች የፈጠራ ባለቤት አሁን ለደረሰበት የእድገት ደረጃ የራሳቸዉን አስተዋጽኦ ያበረከቱ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለዉም፡፡ ምክንያቱም ጥናትና ምርምር /የፈጠራ ስራ/ የሚጀምረዉ ባህላዊ ልምድን መሰረት አድርጎ በመሆኑ ነዉ፡፡ እነዚህ የፈጠራ የመገልገያ ዕቃዎች የህዝቡን የማህበራዊ ግንኙነት ፣ፖለቲካዊ ግቡን ፣የንግዱን ዘርፍ ፣የግብርና ዘርፍ ወዘተ.. ሊገልጹ የሚችሉ የማንነቱ መገለጫዎች ናቸዉ፡፡ ከነዚህ መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹን ዝርዝር በማቅረብ ከምን እንደሚሰሩና ለምን ጥቅም እንደሚዉሉ እናስቀምጣለን፡፡
ሀ. ከእንጨት የተሰሩ
ለ. ከብረታ ብረት የተሰሩ
ሐ. ከቆዳ የተሰሩ
መ. ከቅልና ከስፌት እቃዎች የተሰሩ.
2. ባህላዊ አለባበስና አጋጊያጥ የወረዳዉ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ ዉብና ማራኪ የአለባበስና አጋጊያጥ ስርዓት አለዉ፡፡ በተለይ በወረዳዉ ዉስጥ ከሁለት በላይ ብሔረሰቦች መኖር የእነዚህን ህዝቦች የተለያዩ ዓይነት አለባበስና አጋጊያጥ በቀላሉ ለማየት ያስችለናል፡፡ በተለይ በወረዳዉ ዉስጥ በሚገኙ ዋና ዋና የገበያ ቦታዎች በገበያ ቀን ለአብነትም ያህል በጨፋ ሮቢት፣በአርጡማና በበኬጃ የገበያ ቦታዎች ብቅ ቢሉ የእነዚህን ብሔረሰቦች ማለትም የኦሮሞ፣አማራንና አፋር ልጃገረድን ፣ኮበሌ/ወጣት ወንድ/ ፣ የአዋቂ ወንድ ፣ያገባች ሴት ፣የዱበርቲ/የአዋቂ ሴት/ የአለባበስ ስርዓቶችንና የሁሉም ብሔረሰቦች የጌጥ አጋጊያጥ ማየት ይችላሉ፡፡ ይሄ ዓይነቱ ትዕይንት ህብር ፈጥሮ የህብረተሰቡን ዉብ ባህላዊ አለባበስና አጋጊያጥ ስርዓትና ህ/ሰቡ ስለ ስነ ዉበት ያለዉን ግንዛቤ ስለሚያሳየን ህሊናችን ተመስጦ ዉበትን እንዲያደንቅ ስሜታችንን ይገዙታል፡:
የወረዳዉ ማህበረሰብ በሽመና የተሠሩ የባህል ልብሶችንና የዕደ ጥበብ ዉጤት የሆኑ ጌጣጌጦችን አምርቶ በስፋት የመጠቀም ልምድን ያካበተ ህዝብ ነዉ፡፡ ህብረተሰቡ ራሱ አምርቶ ስለሚጠቀምባቸዉ ከህፃን እስከ አዋቂ ባህላዊ አልባሳትንና ጌጣጌጦችን አዘዉትሮ ሲጠቀም ማየት የተለመደ ነዉ፡፡
2.1 በዋናነት የሚታወቁ ባህላዊ አልባሳት የወንድ ባህላዊ አልባሳት
የሚለበስ ለስጦታ የሚሆን አገልግሎት አለዉ፡፡ በተለይ ወንዶች በወጣትነት ጊዜያቸዉ በእንግድነት በሚድሩበት ቦታ ላይ እንደ ሌሊት ልብስነትም ይለገሉበታል፣
ነዉ፡፡ በበዓል ቀናት፣በዝግጅት ቀናች እና በገበያ ቀናቶች ተዘዉትሮ ይለበሳል፡፡
የሴቶች ባህላዊ አልባሳት፣
ይጠቀምበታል፡፡
3. ሀይማታዊ አልባሳት 1. በአካባቢዉ በሙስሊሙ ህ/ሰብ ዘንድ እንደ ጀለቢያ ፣ጥምጣም፣ቆብ የወንዶች አልባሳት ሲሆኑ ሂጃብ፣ጅልባብ፣ኒቃብ የሚታወቁ ሀይማኖታዊ የሴቶች አልባሳት ናቸዉ፡፡ 2. በአካባቢዉ ክርስቲያን ህ/ሰብ ዘንድ የወንድ ካፖርት ፣አክሊል ፣ቀሚስ ፣ቆብ፣ የሽመና ልብሶች /የሴት ጥበብ…/ የሚታወቁ መንፈሳዊ አልባሳት ናቸዉ፡፡
4. ባህላዊ ጌጣጌጦች የወንድ ጌጣጌጦችና ጥቅሞቻቸው
በተጨማሪም ለወጣት ወንዶች የአንገት ለልጃገረዶች ደግሞ የጸጉር ጌጥ ሆኖ ያገለግላል፡፡ አጠቃቀሙም የተለያዩ ቀለማት ያሉት ፕላስቲኮች በትንሹ በመቀቆራረጥ ወይም የጥይት እርሳሶችን በክር ላይ በማሰር አንገት ላይ ለዉበትነት ይታሰራል፡፡
የሴት ጌጣጌጦችና ጥቅሞቻቸው
|
Artumafursi Copyright© 2009 All Rights Reserved.
Designed by Artumafursi Woreda ICT Core Process