![]() |
![]() |
![]() |
There are no translations available.
1. የቻርተሩ ዓላማ
2. የተቋሙ ስም የአ/ፋ/ወ/ሲ/ሰርቪስ ጽ/ቤት 3 . የጽ/ቤቱ ተልዕኮ · የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ዓላማዎችና ፖሊሲዎች በብቃት መፈጸም የሚችል ተዓማኒነት ያለው፣በግልፀኝነት በተጠያቂኀት መርሆች ላይ ተመሰርቶ ሀገርን፣ህዝብንና ዜጋን የሚያገለግል ጠንካራና ውጤታማ ሲቪል ሰርቪስ መፍጠር፡፡ የጽ/ቤቱ ራዕይ · የበለፀገችና መልካም አስተዳደር የሰፈነባት አርጡማ ፉርሲ ወረዳ ዕውን የሚያደርግ ሲቪል ሰርቪስ በ2010 ዓ.ም በሁሉም የመንግስት ተቋማት ተገንብቶ ማየት፣
የጽ/ቤቱ እሴቶች 1. ሁሉም ተማሪና አስተማሪ መሆን እንደሚገባን እንገነዘባለን፡፡ 2. የስራ ፍቅር፣ ከበሬታና መልካም ስነ-ምግባር መለያችን ይሆናል፡ 3. ለተገልጋዮች / ዜጐች ፍላጐት ቅድሚያ መስጠት፣ 4. ግልጽነትንና ተጠያቂነትን እናሰፍናለን፣ 5. ቅልጥፍናና ውጤታማነትን ማረጋገጥ የጥረታችን ሁሉ መቋጫ መሆኑን እናምናለን፡፡ 6. ፍትሃዊነትን ማስፈን የመልካም አስተዳደር ገጽታችን ዋነኛ አካል መሆኑን እንገልዘባለን፡፡ 7. ለውጥ ናፋቂና አራማጅ እንሆናለን፡፡ የጽ/ቤቱ ተገልጋዮች የወረዳ የመንግስት ተቋማት ፣ የወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ሌሎች ዜጐች
በጽ/ቤቱ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች 1. የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ጥናቶችን ተግባራዊ ማድረግና እንዲተገበሩ ድጋፍ ማድረግ፣ 2. ከመ/ቤቶች የሚቀርቡ የምደባ ቅጥር፤ዝዉዉር፤ደረጃ ዕድገት እና የተለያዩ ጥቅማጥቅም እንዲያገኝ ማድረግ፣ 3. በየደረጃው ለሚገኙ የመንግስት ተቋማት በሰው ኃይል ስምሪትና በለውጥ ስራዎች አፈፃፀም ዙሪያ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ 4. በለውጥ ሰራዊት ግንባታና አፈፃፀም ዙሪያ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ 5. የድጋፍና ክትትል ግብረ መልሶችን ማሳወቅ፣ 6. የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ክፍተት የዳሰሳ ጥናት ማጥናት 7. የተለያዩ የአቅም መገንቢያ ስልጠናዎችን መስጠት 8. በስልጠናዎችና ኘሮግራሞች አፈፃፀም ላይ የፋይዳ ጥናት ግምገማ ማድረግ፣ 9. ከመ/ቤቶች የሚቀርቡ የስራ ልብስ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ጽ/ቤት ማሳወቅ፣ 10. ከመ/ቤቶች ለሚቀርቡ የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ ያካተተ ጥያቄዎችን ለዞን ግብአት መስጠት፣ 11. በመመሪያዎች ዙሪያ በጹሁፍ በቃልና በስልክ ለሚቀርቡ የማብራሪያ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት፣ 12. በመንግስት ድጋፍ ትምህርታቸውን አጠናቀው በመ/ቤታቸው ቦታ ላልተገኘላቸው ምሩቃን የስራ ምደባ መስጠት፣ 13 . ከኃላፊነት ለሚነሱ ተሷሚወችና ምደባ፣ላላገኙ ሰራተኞች የስራ ምደባ መስጠት፣ 14. የረጅም ጊዜና የአጭር ጊዜ ስልጠናዎችን ማስተባበር 15. የጡረታ ማራዘም ጥያቄዎችን ተቀብሎ ለዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ማስተላለፍ 16. ሙያዊ ድጋፍ ለሚጠይቁ አካላት ሙያዊ ድጋፍ መስጠት፣ 17. የመንግስት ሰራተኞችን ስታቲክሳዊ መረጃ በዓመት አንድ ጊዜ መስጠት፣ 18. የዲስኘሊን ጉዳዮችን ተቀብሎ መመርመርና ማጣራት የውሣኔ ኃሣብ መስጠት፣ 19. የሰው ኃይል አስተዳደር ተግባራት ይፃፍልኝ ጥያቄዎችን ተቀብሎ መፈጸም፣ 20. በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ምላሽ መስጠት፣
አጠቃላይ የጥራት መርሆቻችን በስታንዳርዱ ላይ የተገለፁ አገልግሎቶችን በሚከተሉት አጠቃላይ የጥራት መርሆች ላይ ተመስርተን እንሰጣለን፡፡ ግልፅነት የምንሰጠው ማንኛውም አገልግሎት ባስቀመጥናቸው ስታንዳርዶች፣ቅድመ ሁኔታዎች፣መመሪያዎችና ማንዋሎች ላይ መሰረት በማድረግ ለደንበኞቻችን ፍጹም በሆነ መንገድ ይሰጣል፡፡ ቶሎ ምላሽ መስጠት ደንበኞችን ባስቀመጥነው ስታንዳርድ መሰረት ምንም ሳየጉላሉ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ ተከታታይነት ያለው መሻሻል ስራዎቻችንን በየዕቅድ ዘመኑ በመገምገም፣ክፍተቶቻችንን ለመሙላት ተከታታይነት ያለው ማሻሻያ እናደርጋለን፡፡
ተደራሽነት አገልግሎታችን በስራ ሂደቶቻችን የስራ ሂደት ጥናት ባስቀመጥነው ተደራሽ ግብ መሰረት እስከታችኛው የአስተዳደር እርከን ድረስ እንዲደርስ ይደረጋል፡፡ አሳታፊነት የአገልግሎታችን ተጠቃሚ የሆኑ ተገልጋዮቻችንና ያገባኛል ባዮችን በዕቅድ፣በአፈፃፀማችንና በድጋፍና ክትትላችን ወቅት እናሳትፋለን፡፡ ቅድመ ሁኔታዎች ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት የተለያዩ ጥናቶችን አስቀድመን በማካሄድ በመረጃ ላይ ተመስርተን ችግሮችን እንከላከላለን፡፡ ተገልጋይ ተኮር የምንሰጣቸው አገልግሎቶች በተገልጋዮች ፍላጐት ላይ የተመሰረቱ ይሆናሉ፡፡
ዉጤታማነት አገልግሎት አሰጣጣችን የመምረያዉን ተልጠዕኮና ራዕይ በሚያሳኩ ተግባራት ላይ ያተኮረ ይሆናል፡፡
የተገልጋዩች መብቶች ሀ. በመምረያዉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን የማግፕት መብት ፡ ለ. መረጃ የማግኘት መብት ፡ ሐ. በመምረያዉ አሰራር ላይ አስተያየት የማቅረብ መብት ፡ መ. ቅሬታ የማቅረብ መብት ፡ ለተገልጋዪቻችን የምንገባዉ ቃል ሀ. የምንሰጣቸዉን አገልግሎቶች በስታንዳርዳችን መሰረት እንፈጽማለን ለ. ዕቅዳችንን ሳናንጠባጥብ እንፈጽማለን፡ ሐ. አገልግሎታችን በተገልጋዩቻችን ፍላጎት ላይ የተመሰረት ነዉ፡ መ. ለተገልጋዩች ፍትሃዊ ፡ ቀልጣፋና ዉጤታማ አገልግሎቶች እንሰጣለን፡ ሠ. ተገልጋዩቻችንን በቅንነትና በታማኝነት እናገለግላለን፡
አስተያየት የግብአትና የተሳትፎ ሂደት አስተያየትና ግብዓት ሀ. ተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ በአካል፣በተዘጋጀ የሀሳብ መስጫ ካርድ፤ በሃሳብ መስጫ መዝገብና ሳጥን እና የተለያዩ የምክክር መድረኮችን በመጠቀም አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡ ለ. ከተገልጋዮች የተገኘውን አስተያየት በመገምገም እንደ ግብዕአት በመጠቀም ግብረ መልስ እንሰጣለን፡፡ የተሳትፎ ሂደት በበኩር ጋዜጣና በሌሎች የክልሉ ሚዲያዎች በመጠቀም እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ ወረዳ በሚያዘጋጀው የምክክር መድረክ በአገለግሎት አሰጣጣችን ላይ ተገልጋዮችን በቀጥታ እናሳትፋለን፡፡ የቅሬታ አቀራረብ ሂደት ተገልጋዩ ባገኘው አገልግሎት ካልረካ ቅሬታውን አገልግሎቱን ለሰጠው ባለሙያ የቅርብ ኃላፊ ማቅረብ የሚችል ሲሆን በዚህም ካልረካ ለጽ/ቤቱ ኃላፊ አገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታ ሰሚ ባለሙያው ያቀርባል፡፡ ባለሙያውም የአሰራር ሂደቱን ተከትሎ ለቀረበው ቅሬታ ምላሽ ይሰጣል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለመገናኛ ብዙሃንና አግባብ ላላቸው አካላት ማሳወቅ ይችላል፡፡
የክትትልና ግምገማ ስርአት vጽ/ቤቱ በቻርተሩ ላይ በተቀመጡት መሰረት ዜጋው አገልግሎት ስለማግኘቱ በክትትልና ድጋፍ ያረጋግጣል፡፡ vበዚህም ኃላፊነት ያለባቸው የሰራ ሂደት መሪዎችና ፈፃሚዎች በቻርተሩ መሰረት ስለመፈጸማቸው በለውጥ ሰራዊት አግባብ በየሳምንቱና በየወሩ በመገምገም ሪፖርት ለተቋሙ የበላይ አመራር ያቀርባል፡፡ vበየወቅቱ የቀረቡት የክትትልና የግምገማ ሪፖርቶች ላይ በመመስረት የእርምትና የማስተካከያ እርምጃ ይወሰዳል፡፡ vየተገልጋዮች መድረክ መደራጀታቸውንና ስራ ላይ መዋላቸው ይረጋገጣል፡፡ vበገለልተኛ ወገን የተገልጋዮች እርካታ መኖሩን መደረጉን ያረጋግጣል፡፡ vየቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓት በአግባቡ መዘርጋቱን ያረጋግጣል፡፡
የመረጃ ማስተላለፊያ መንገዶች ሀ. በተቋሙ የሚሰጡ የመረጃ አይነቶች አዋጅ፣ደንቦች፣መመሪያዎች፣ማንዋሎች፣የጥናት ሰነዶች፣የወረዳዉን መንግስት ሰራተኞች ስታትስካዊ መረጃ፣የተለያዩ ኘሮግራሞች፣እና የኘሮጀክት ሰነዶች፣ እቅዶችና ሪፖርቶች፣መግለጫዎች፣መጽሔቶችና በራሪ ጹሁፎች
ለ. የመረጃ ማስተላለፊያ ዘዴዎች በበራሪ ጹሁፎች፣በመጽሔት፣በፋክስ፣በስልክ፣በፖስታ ቤት፣በመረጃ ማዕከል አማካኝነት፣በአካል፣የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሪፖርቶች፡-በፋክስ፣በፖስታ ቤት፣ በመረጃ ማዕከል አማካይነት፣በአካል፣በስልክ፣ መደበኛ የተገልጋይ መድረኮች፡- በአካል በመገኘት ሁሉም ለለውጥ ይሁን! |
Artumafursi Copyright© 2009 All Rights Reserved.
Designed by Artumafursi Woreda ICT Core Process