Blue Joomla Templates

ጎብኝዎች

mod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_counter
mod_vvisit_counterToday51
mod_vvisit_counterYesterday46
mod_vvisit_counterThis week51
mod_vvisit_counterLast week175
mod_vvisit_counterThis month809
mod_vvisit_counterLast month1300
mod_vvisit_counterAll days14723

We have: 39 guests online
Your IP: 18.116.52.117
Mozilla 5.0, 
Today: Jun 30, 2024

የአለም ሰዓት አቆጣጠር

Online User

We have 39 guests online

Archieved Content

Print E-mail

 

የወረዳዉ አጠቃላይ መረጃ

አርጡማ ፉርሲ ወረዳ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ዞን መስተዳድር ካሉት ወረዳዎች አንዷ ስትሆን ከአዲስ አበባ ከተማ በአገሪቱ ሰሜን አቅጣጫ በ300 ኪ.ሜ ርቀት፣ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር በአገሪቱ ምስራቅ አቅጣጫ በ580 ኪ.ሜ ርቀት፣ ከዞኑ ዋና ከተማ ከሚሴ በአገሪቱ በስተደቡብ አቅጣጫ በ25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ የወረዳችን አዋሳኞች በሰሜን ደዋ ጨፋ ወረዳ ፣በደቡብ ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፣በምስራቅ አፋር ክልል፣በምዕራብ ከአንፆኪያ ገምዛ ወረዳዎች ጋር ይዋሰናል፡፡ ወረዳዉ በ24 የገጠር ቀበሌዎች እና በ 3 የከተማ ቀበሌ የተዋቀረ ወረዳ ነዉ፡፡

የወረዳዉ ቆዳ ስፋትም 108181 ሄክታር ነዉ፡፡ የብሔረ ብሔረሰቦች መረጃም ስናይ 98% ኦሮሞ ብሔር እንዲሁም 2% ደግሞ አማረኛ ተናጋሪ ብሔሮች ሲኖሩ የሃይማኖት አይነቶችም 97% እስልምና ሃይማኖት ተከታዮች 3% ደግሞ ክርስትና እምነት ተካታዮች በወረዳዉ ዉስጥ ይኖራሉ፡፡ የወረዳዉ ህዝብ ብዛትም በገጠር ወንድ 48617 ሴት 50134 ድምር 98751 ሲሆን በከተማ ወንድ 5587 ሴት 5343 ድምር 10930 በጠቅላላዉ 109681 ህዝቦች በወረዳዉ ዉስጥ ይኖራሉ፡፡ ከጠቅላላዉ ነዋሪ 49.4% ወንዶችና 50.5% ሴቶች ሲሆኑ ወረዳዉ ህዝብ 49442 አምራች ኃይል ዕድሜዉ ከ15-64 ዓመት ነዉ፡፡ የወረዳዉ ዋና ከተማዋም ጨፋሮቢት ትባላለች፡፡

 

 

የወረዳዉ መልክዓ ምድር አቀማመጥ ሁኔታ

የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ የቆዳ ስፋት 108181 ሄክታር ሲሆን የወረዳዉ መሬት አቀማመጥም 38% ሜዳማ፣ 28.5% ተራራማ፣ 25.5% ወጣ ገባ፣ 6.6% ሸለቆአማ ሲሆን 4.4% ደግሞ ረግረጋማ በቆዳ ሽፋን አቀማመጥ ተሸፍኗል፡፡ የአየር ንብረቷም 76% ቆላማ እና 24% ወይና ደጋማ ነዉ፡፡ የወረዳዉ የሙቀት መጠን ከ15-350c ነዉ፡፡ ከፍታ ከባህር ወለል በላይ ከ1200-2000 ሜትር ከፍታ ሲኖረዉ የወረዳዉ አመታዊ የዝናብ መጠንም ከ600- 900 ሚ.ሊ ነዉ፡፡

የወረዳዉ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ

የወረዳችን ህዝብ የኑሮ ሁኔታ ስናይ 89% በግብርና የሚተዳደርና 11% ደግሞ በመንግስት ስራ እና በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተዉ የሚኖሩ ናቸዉ፡፡ በወረዳዉ በብዛት የሚመረቱ የምርት አይቶች ማሽላ፣ጤፋ፣በቆሎ፣ወዘተ ናቸዉ፡፡ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ (FTC) ብዛት 18 ነዉ፡፡ የእንስሳት ጤና (ህክምና) ጣቢያዎች ብዛት ደግሞ 6 ናቸዉ፡፡ የቀንድ ከብቶች ብዛት 65233 የጋማ ከብት ብዛት 6720 ነዉ፡፡ የቆዳ ስፋት 108181 ሄክታር ሲሆን ለእርሻ ዋለ መሬት 11923 ሄ/ር፣ በደንና ቁጥቋጦ የተሸፈነ 59333 ሄ/ር ፣ በውሀ የተሸፈነ 3793 ሄ/ር፣ ለኮንስትራክሽን የዋለ 8495 ሄ/ር ፣ ለግጦሽ የዋለ 10153 ሄ/ር፣ ገላጣ መሬት 14444 ሲሆን ለኢንቨስትመንት የዋለ 40 ሄ/ር ነዉ፡፡ የወረዳዉ አፈር አይነት ቡናማ አፈር 15%፣ ቀይ አፈር 7%፣ ሸክላ አፈር 76%፣ ሌላ የአፈር አይነት 2% ነዉ፡፡

የወረዳዉ የገጠር መንገድ ተደራሽነት ወይም ሽፋን ያለበት ሁኔታ ስናየዉ በወረዳዉ ዉስጥ ካሉ 24 የገጠር ቀበሌዎች ዉስጥ 19 ቀበሌዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የደረሠባቸዉ ሲሆኑ ቀሪዎቹ 5 ቀበሌዎች ደግሞ በእቅድ ተይዘዉ እየተሠራላቸዉ ይገኛል፡፡ የወረዳዉ የገጠር መንገድ ሽፋን ወይም ተደራሽነት 80% ላይ ይገኛል፡፡

የወረዳዉ ማህበራዊ ሁኔታዎች

በትምህርት መስክ የትምህርት ተቋማቶች ብዛት የመጀመሪያ ደረጃ የመጀመሪያ ሳይክል (1-4) ብዛት 6፣ የመጀመሪያ ደረጃ የሁለተኛ ሳይክል(5-8) ብዛት 43፣ የሁለተኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሳይክል (9-10) ብዛት 02፣ የሁለተኛ ደረጃ ሁለተኛ ሳይክል ወይም መሰናዶ (11-12)ብዛት 01፣ አንድ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኬሌጅ በወረዳዉ ዉስጥ ይገኛሉ፡፡ ይህም እንዳለ ሆኖ የየሳይክሉ የት/ት ሽፋን ስንመለከት ደግሞ ከ1-8ኛ 96% ፣ከ9-10ኛ 58.96% ፣የማህበረሰብ አ/ቅድመ መደበኛ 4-6 ዓመት 96.94% ፣ ከ11-12ኛ 4.88% ላይ ይገኛሉ፡፡

በወረዳው ውስጥ ያሉ የጤና ተቋማት ብዛት

ደረጃዉን የጠበቀ ጤና ጣቢያ ብዛት 6 ፣ ጤና ኬላ ብዛት 22፣ ፋርማሲ ብዛት 3 ነዉ፡፡ የጤና ሽፋን በጤና ጣቢያ ደረጃ ተደራሽነት 100% የጤና ሽፋን/ተደራሽነት በጤና ኬላዎች ደግሞ 92% ነዉ፡፡ የወረዳዉ የጤና ስራን ስናይ በወረዳችን ጤና ስራ ዋናዉ የእናቶች ጤናን በመጠበቅ በወሊድና በፋሚሊነግ/የቤተሰብ ምጣኔን በሰፊዉ ትኩረት በመስጠት እየተሠራ ይገኛል፡፡

 

 
free pokerfree poker

Slide Show

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5
JT-SlideShow-Footer

ስለ ድረ-ገፃችን

ስለ ድረ-ገፃችን
 

Artumafursi Copyright© 2009 All Rights Reserved.

Designed by Artumafursi Woreda ICT Core Process